Friday, March 8, 2013

አቶ አልአዛር ፥ "ከመቃብሮት ይነሱና" በቅርበት የሚያውቁትን ይጻፉ


            አቶ አልአዛር ፥ "ከመቃብሮት ይነሱና" በቅርበት የሚያውቁትን ይጻፉ

ግልጽ መልዕክት ለአቶ አልአዛር ኬ

    ለዚህ መጣጥፌ ምክንያት የሆነኝ አልኣዛር ኬ የተባሉ ሰው በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በእስራኤል ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን (ቤተእስራኤላውያን) በተለያየ ጊዜ የጻፎቸውን መልእክቶች ተመልክቼ ነው። ከመነሻው ጽሑፋቸው ባጠቃላይ ከ"ሀ" እስከ "ፐ" ያነጣጠረው ትችት ላይ ነው። የመጀመሪያ አሳባቸው ቤተእስራኤላውያን በእስራኤል የዘር መድሎ እየደረሰባቸው እንደሆነ ሲሆን፤ ሁለተኛው የእስራኤል መንግስትም ሆነ ሕዝብ እስራኤል ዘረኖች እንደሆኑ ለማሳየት መኩረዋል። አቶ አልአዛር ትንሽ ጫፍ ይይዙና "በሬ ወለደ" ድርሰታቸውን ይሞነጫጭሩልናል። በዚህ ላይ ለትችት ታጥቀው የሚነሱ መልካም ነገርን እንኳን በተጣመመ እይታ የሚመለከቱ አይነት ጸሀፊ ናቸው፤ አቶ አልአዛር፥ ለአዲስ አድማስ ታዳሚዎች ሊያስተላልፉት የፈለጉት መልእክት ለራሶት እንኳን የማይገባዋት እንቶፎንቶ የበዛበት ጽሁፍ ነበር። ቤተእስራኤላውያን በሀገረ እስራኤል ሲኖሩ ቤት ሲገዙ፣ የተሰማሩበት የስራ ዘርፍና በነጭ አይሁዳውያንና በእስራኤል መንግስት ይደርስባቸዋል ያሉትን ዘረኝነት ጽፈል። እንደ እኔ እምነትና እይታ በእስራኤል ሀገር በጣት የሚቆጠሩ ዘረኛ ሰዎችና ድርጅቶች እንዳሉ የማይካድ ሐቅ ነው። ይህ ማለት ግን እስራኤላውያን (ነጭ አይሁዳውያን) እና መንግስታቸው በቤተእስራኤላውያን ላይ የዘር ወይም የቀለም መድሎ ይፈጽማሉ፣ቤተእስራኤላውያንን በዘረኝነት አግለዋቸዋል ለማለት አያስደፍርም። ቤተእስራኤላውን እግራቸው እስራኤልን ከረገጠባት ጊዜ አንስቶ እንደማንኛውም ዜጋ እኩል መፍትና ግዴታ አላቸው። ለቤተእስራኤላውያን ብቻ ተብሎ የሚቋቋም ት/ቤት ወይም የስራ መስክ ሊኖር አይችልም፤ አልያም ከሌላው ህብረተሰብ በተለየ ሁኔታ ያለምንም መመዘኛ በከፍተኛ ተቋማት ገብተው ይማሩ ማለት አይቻልም። በስራ ዘርፉም ቢሆን እንደዛው ነው።
    አቶ አላዛር ለቤተ እስራኤላውያን ተቆርቁረው ነው እንዳይባል በየመሃሉ የሚሰነዝሮቸው ጋጠወጥ ንግግሮት ለቤተእስራኤላውያን ያሎትን አመለካከት የሚያሳይ ነው፤ ስለእርሶ ለማወቅ ደግሞ ብዙ ሳልሄድ የአእምሮት ጭማቂ የሆኑ ጽሁፎች መመልከት በቂ ነበር። "በፍሪያቸው ታውቋቸዋላችሁ" እንደሚል መጽሐፉ ለትችትና ለማጥላላት ታጥቀው እንደተነሱ ያመለክታሉ። ይህ ደግሞ እንደ አዲስ አድማስ ላሉ የሕዝብ ጋዜጦች ላይ ለመጻፍ ሚዛኑን የሚያሞሉ አይነት ጸሐፊ አልነበሩም። እባኮት ያልበላዎትን ከሚያኩና ደርሶ አዋቂ ለመምሰል ከዌብሳይት ላይ እየለቃቀሙ የማያውቁትን ከመሞነጫጨር ይልቅ በዙሪያዎት ያሉ፣ በአይኖት የሚያዩትን፣የዕለት ከዕለት የወገኖ ኑሮ፣ በሀገሮ ስለሚካሄድ ዘረኝነት፣ ጎሰኝነትና የፍትህ ጉድለት ቢጽፉ ይሻሎታል። በዚህም ላይ ሌላ አላማና ተልእኮ ካለህ እርምህን አውጣ ለመዝራት የመኮርከው እንክርዳድ በጭንጫ እንደወደቀ ቁጠረው ምክንያቱም አብዛኛው ቤተ እስራኤላዊ እርሶን አይሰማዎትም።
    የእስራኤል መንግስት ዘረኞችን የሚደግፍ አዋጅ ሲያወጣ አልታየም ወይም የዘር መድሎ ከሚፈጽሙት ግለሰቦችና ተቋማት ጋር ተባባሪ ሲሆን አላየንም አልሰማንም። በተቃራኒው በሕግ ዘረኞች የሚቀጡበት አርቅቆ በፍርድ ቤት ብዙዎች ሲቀጡ እያየን ነው። የእስራኤል መንግስት የቤተእስራኤላውያን ጥላቻ ካለበት ለምን ከገጠራማዋ ኢትዮጵያ አውጥቶ ወሰዳቸው ማንስ አስገደደው ? አቶ አላዛር ዘረኞች እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ አርባ ዓመት ታላቆን ኢትዮጵያን የመራች ንግስት ዮዲትንና መንግስቷን 40 ዓመት ሙሉ ቤተክርስቲያን ስታቃጥል የኖረች ብለው የሚኮኑኖት ናቸው። ለመሆኑ ያኔ በዛ ዘመን የነበረው የቤ/ክ ብዛት ለማቃጠል አርባ ዓመት የሚፈጅ ነበር? ወይስ ምንድነው ? ቤተእስራኤላውያን በኢትዮጵያ ሲኖሩ በተራራማ ቦታ ላይ ይሰፍሩ የነበረው ወደው ይመስሎታል፣ ከዘረኞች ጥቃት ለመዳን ነበር። ዛሬም ድረስ በእንደርሶ አይነት ሰዎች እየተናቁ እየተሰደቡ ነው። ወይስ እነዚህ ሰዎች ከእበት ልቅላቂ ቤት ወጥተው ባማረ ሕንጻ መኖራቸው፣ ልጆቻቸው ከማህለ ሕጻናት እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደረጃቸውን በጠበቁ ትምህርት ቤቶች፣ ብቁ በሆኑ መምህራን፣ በምርጥ ስርዓተ ትምህርት መማራቸው፤ አነሰም በዛም እንደ ደረጃቸው ሰርተው የልፋታቸውን ዋጋ መቀበላቸው፤ በማንነታቸው በሃይማኖታቸው ሳይሳቀቁ መኖራቸው ምነው እንደዚህ አንገበገቦት ?
    አቶ አላዛር ነጭ ይሁዳውያንን እርሶ ከሚያወሩባቸው በላይ ቤተእስራኤላውያን ያውቋቸዋል። ከእነርሱ ጋር ተምረው፣ በውትድርና እጅለእጅ ተያይዘው፣ ለስራ አብረው ተወዳድረው ፣አብረው ሰርተው ፣ ነጮቹ የቅርብ አለቆቻቸው ሆነው ፣እነርሱም አለቆቻቸው ሆነው፣የቤተእስራኤላውያን ልጆች ከነጮቹ ልጆች ጋር አብረው እየተማሩና እያደጉ ምኑን ልንገሮት ይህን ሁሉ አብረው ያሳለፉና እያሳለፉ ያሉ ህዝቦች ናቸው። ታዲያ አንዳንድ ዘረኝነት የተጠናወታቸው ግለሰቦችና አዳንድ ተቋማት እንዳሉ የማይካድ ሀቅ ነው። እነዚህን ነው ቤተእስራኤላውያን እየተቃወሙ ያሉት። ከተቋውሞአቸውም ጎን ብዙሃኑ ነጭ ይሁዳውያን ተሰልፈው ይገኛሉ።




No comments:

Post a Comment