Thursday, July 7, 2016

የጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ ጉብኝት በአፍሪካ



በእራኤል መሪዎች የሀገራት ጉብኝት ታሪክ ታይቶ የማይታወቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ የአፍሪካ ጉብኝት አራት አውሮፕላኖችንና ልዩ የደህንነት ጥበቃን ያካተተ ነው። አክራሪው የእስራኤል የግራ ክንፍ ፓርቲ “ሜሬጽ” ሊቀመንበርና ሃቬር ክኔሴት (የፓርላማ አባል) የሆኑት ወ/ሮ ዛሃቫ ጋሎን በናታንያሁ የፍሪካ ጉዞ ላይ አስታየት ሲሰጡ “ የአፍሪካ ጉብኝቱ አስፈላጊ ነው ፤ ነገር ግን እኔን የሚያሳስበኝ የእርስበርስ ግጭት በበዛባት አፍሪካ የእስራኤል የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች መኖራቸው ነው ” ብለዋል።


 ናታንያሁ ከባለቤታቸው ጋር በምሥራቅ አፍሪካ ለአራት ቀናት የሚያደርጉትን ጉብኝት በኡጋንዳ፣ በሩዋንዳ፣ በኬንያና በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝት ወደ 150 የሚጠጉ የእስራኤል ልዑካንን ያካተተ ነው ። ለደህንነታቸውም የሚያስፈልጉ ነገሮች በልዩ ሁናቴ የተዛጋጀ ሲሆን፤ ጉብኝቱ በሁለት ሲቪል አውሮፕላኖችና በሁለት ሄርኩለስ አውሮፕላኖች ይከናወናል ። ባለፈቱ ሳምንታት የናታንያሁ መንግሥት ለእስራኤልና አፍሪካ ግንኙነት ወደ 50 ሚሊዮን ሼኬል ያጸደቀ ሲሆም ከዚህ ውስጥም 28 ሚሊዮኑ ለናታንያሁ የአፍሪካ ጉብኝት ተመድቧል ። ናታንያሁ ከአፍሪካ ጉብኝታቸው አንድ ቀን ቀደም በሎ በካቢኔ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ “ነገ ታሪካዊውን የአፍሪካ ጉዞ እጀምራለው ” ያሉት ጠ/ሚ ናታንያሁ ለአለፉት አሥርተ ዓመታት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በዚያ እንዳልነበረና በኡጋንዳ ከሰባት የአፍሪካ መሪዎች ጋር እንደሚያናግሩ በመቀጠልም በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ግቡኝት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ። ከ30 ዓመታት በኋላ አንድ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትን ሲጎበኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ የመጀመርያ ናቸው።


ከፍተኛ በጀት የተያዘለት፣ የስራኤል ጦር ኃይል ተወካዮችን ፣ ባለሃብቶችና የንግድ ማህበረሰብ ያካተተው የናታንያሁ የአፍሪካ ጉብኝት ሀገራቸው ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው በሰፊው እየተነገረ ነው ። ይህ የጠቅላይ ምንስቴሩ ግቡኝት እስራኤልን ወደ አፍሪካ፤ አፍሬካን ደግሞ ወደ እስራኤል የመመለስ እቅድን ያነገበ ነው ተብሎለታል። ይህ የናታንያሁ የአፍሪካ ጉዞ ለእስራኤል ዓለም አቀፍ ጥምረት ታላቅ አንድምታ እንደሚኖረው እየተነገረ ነው ። እስራኤል በአሁን ወቅት እያከናወነችው የሚገኘው ከሩሲያ ፣ ከላቲን አሜሪካና የአፍሪካ አህጉር ጋር የምታደርገው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ግንኙነት ሀገሪቱ በእስያ ውስጥ ያላትን የበላይነት ለማሳደግ ይጠቅማታል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ ኡጋንዳ በሚያደርጉት ጉብኝት የዛሬ 40 ዓመት ንብረትነቱ የኤር ፍራንስ የሆነ የበረራ ቁጥር 189 ኤር ባስ ኤ-300 የመንገደኞች አውሮፕላን በሁለት ፍልስጤማውያን ሸምቅ ተዋጊዎች ከሁለት ጀርመናውያን ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን ተጠልፎ በእስራኤል ኃይል ታጋቶቹ የተለቀቁበትን ምክንያት በማድረግ ለሚደረግ ዝግጅት ላይ “ራም” የሚባለው የእስራኤል አየር ኃይል ጀት ወደ ኢንቴቤ ያመራል ። በስነሥርዓቱ ላይ የእስራኤል ከፍተኛ የጦር ኃይል አላፊዎች ፣ በወቅቱ በኦፕሬሽን ኢንቴቤ ውስጥ ተሳትፈው የነበሩ፣ ታጋቾችና ዘመዶቻቸው በዝግጅቱ ላይ ይገኛሉ ።

ኦፕሬሽን ኢንቴቤ ፦ ከእስራኤል ቴል አቪቭ የተነሳው ንብረትነቱ የኤር ፍራንስ

የሆነ የበረራ ቁጥር 189 ኤር ባስ ኤ-300 የመንገደኞች አውሮፕላን አቴንስ አርፎ በመቀጠል ወደ ፓሪስ ሲንቀሳቀስ ሁለት ፍልስጤማውያን ሸምቅ ተዋጊዎች ከሁለት ጀርመናውያን ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን አውሮፕላኑን ይጠልፉና አቅጣጫውን ያስቀይሩታል፡፡ ሊቢያ ቤንጋዚ አረፈ ያሳርፉታል ። በሊብያም ነዳጅ ከሞላ በኋላ በማግስቱ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲጓዝ ያደርጋሉ።
 

 በኢንቴቤ አውሮፕላን ማረፊያም በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ከ248 መንገደኞችና 12 ሠራተኞች መካከል 106 እስራኤላውያንን በማገት ሌሎቹን በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን ታጋቾች ይለቋቸዋል ። አጋቾቹ በእጃቸው ያሉትን እስራኤላውያን መንገደኞችን ወደ ኢንቴቤ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናሉ በመውሰድ በእስራኤልና በሌሎች ሀገሮች ታስረው የሚገኙ 53 የፍልስጤማውያን ሽምቅ ተዋጊዎች በሶስት ቀናት ውስጥ እንዲለቀቁ ካልሆነ ግን በእጃቸው ያሉትን እስራኤላውያን እንደሚገሉ ያስጠነቅቃሉ ። የእስራኤል መንግስትና ወዳጅ መንግስታት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በወቅቱ የኡጋንዳ መሪ የነበረውን ኢዲ አሚንን ለማግባባት ጥረት ቢደረግም ሊሳካ ልቻለም ። ዲፕሎማሳዊው እንቅስቃሴም ለውጥ ማምጣት አልቻለም ነበር፡፡ የሶስት ቀን ቀነ ገደቡም ሊጠናቀቅ ሲል እስራኤል ከአጋቾቹ ጋር መደራደር እንደምትፈልግ ትገልጽና ቀነገደቡ በተጨማሪ ሶስት ቀናት ይራዘማል። ድርድሩም ሊሰምር አልቻለም በእነዚህ ቀናት ውስጥ እስራኤል ሌላ ታጋቾቹን ማስለቀቂያ መንገድ ትቀይሳለች ።ይህም የመጨረሻው ምርጫ ነበር።



No comments:

Post a Comment